የዐፄ ዳዊቷ በራራ፤ በደግማዊ ምኒልክ ዘመን እንደገና የታደሰችው አዲስ አበባ

0
0 0
Read Time:2 Minute, 10 Second

የዐፄ ዳዊቷ በራራ፤ በደግማዊ ምኒልክ ዘመን እንደገና የታደሰችው አዲስ አበባ በወያኔና በኦነግ ዘመን በግማሽ ጠበበች እንጂ ፈጽሞ አልሰፋችም!


ታከለ ኡማ ሳይፈጽመው በመቅረቱ የተፀፀተበትንና ለኦሮሞ ብሔርተኞችን ይቅርታ የጠየቀበትን አዲስ አበባን ፊንፊኔ የማድረግ ቀሪ የኦሮሙማ አላማ እንድታሳካ በዐቢይ አሕመድ ተሰይማ በአዲስ አበባ ሕዝብ ላይ የተጫነችዋ ተረኛዋ ከንቲባ አዳነች አበቤ በትናንትናው እለት ከአገዛዙ ልሳን ጋር ባደረገችው ቃለ መጠይቅ ጀሞ 3፣ ጀሞ 3፣ ሳሚት፣ ቦሌ አያት 5፣ ቦሌ፣ አያት 3 እና ቦሌ 4 ከኢሕአዴግ ዘመን በፊት አዲስ አበባ አልነበሩም ስትል በድፍረት ተናግራለች። ቃለ መጠይቅ ያደረገላት “ጋዜጠኛ”ም መደዴ ካድሬ ስለሆነ ተከታይ ጥያቄ ሳያቀርብላት የፈለገችውን አስተጋብታ እንድታልፍ አግዟታል።
በኅሊና እስረኞች በእነስክንድር ነጋ ላይ የግፍ ክስ የመሰረተችዋ እና ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም “አዳነች አቤቤን ዝም ብዬ ሳያት ራሷ ፍትህ ትመስለኛለች”፤ ያሏት አዳነች እንዳለችው በእውነት አዲስ አበባ በወያኔና በኦነግ ዘመን ሰፍታለችን? በፍጹም! አዲስ አበባ በፋሽስት ወያኔና በናዚ ኦነግ ዘመን በግማሽ ጠበበች እንጂ ፈጽሞ አልሰፋችም!


ከታች የታተመው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ካርታ የደርግ አገዛዝ መጋቢት 6 ቀን 1968 ዓ.ም. በነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር 25 ላይ ያወጣው የወቅቱን የአዲስ አበባ ከተማ ስፋት የሚያሳይ ካርታ ነው። ካርታው የታተመው የአዲስ አበባ ከተማ ካርታ የከተማ ቦታ የኪራይና የከተማ ቤት ግብር አዋጅ ቁጥር 80/1968 ዓ.ም.ን ለመደንገግ ከመጣው አዋጅ ጋር ነው።
ካርታና አዋጁን ፈርሞ በነጋሪ ጋዜጣ መጋቢት 6 ቀን 1968 ዓ.ም. እንዲወጣ ያደረገው የኦሮሞ ተወላጁ የወቅቱ የአዲስ አበባ ከንቲባ መኮንን ሙላት ይባላል። በአዋጁ መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ የወቅቱ ስፋት 122,000 ሄክታር ነው። ይህ የአዲስ አበባ ካርታ በቀዳማዊ ኃይለ ዘመነ መንግሥት ከነበረው የአዲስ አበባ ስፋት ጋር አንድ አይነት ነው። በፋሽስት ወያኔና በናዚ ኦነግ ዘመን ግን የአዲስ አበባ ከተማ ስፋት 54,000 ሄክታር ነው ተብሏል። ይታያችሁ! አዳነች አዲስ አበባን ሰፍታለች የምትለን በግማሽ የጠበበችውን 54,000 ሄክታሯን ግማሽ አዲስ አበባን ነው።


ከካርታው ላይ በግልጽ እንደሚታየው በፋሽስት ወያኔና በናዚ ኦነግ ዘመን «ኦሮምያ» በሚል የተፈጠረው ክልል አንድ ዞን የተደረገው «ፊንፊኔ ልዩ ዞን» አካል የሆነው ገፈርሳ በ1968 ዓ.ም. በወጣው አዋጅ የአዲስ አበባ ከተማ አንዱ ክፍለ ከተማ ነበር። በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመንም እንደዚያ ነበር። «የፊንፊኔ ልዩ ዞን» ተብሎ ኦሮምያ ክልል ውስጥ የተካተተው መሬት የአዲስ አበባ ክፍል ነበር።


አዳነች ጀሞ 3፣ ጀሞ 3፣ ሳሚት፣ ቦሌ አያት 5፣ ቦሌ፣ አያት 3 እና ቦሌ 4 ከኢሕአዴግ ዘመን በፊት የአዲስ አበባ ክፍሎች አልነበሩም ስትል ያደረገችው ንግግር በዘመኗ ልትሰራው ያሰበችውን የኦሮሙማ አላማ ጠቋሚ ነው። “የፊንፊኔ ከተማና የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ከምርጫው በፊት ምላሽ ማግኘት አለበት” እያሉ ስለሆነ የአዳነች ንግግር እነዚህን አካባቢዎች ወዴት ለማካለል እንዳሰቡ ፍንጭ የሚሰጥ ነው።


የአዲስ አበባ ከተማ ወደ ቀድሞ ይዞታው መመለስ ይኖርበታል። አዲስ አበባ በፋሽስት ወያኔና በናዚ ኦነግ ዘመን የተወሰደባትን ገፈርሳ ክፍለ ከተማና የተቀሩት ከአዲስ አበባ ተወስደው «የፊንፊኔ ልዩ ዞን» የተደረጉት ክፍለ ከተሞቿ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴና በደርግ ዘመን እንደነበረው ተመልሰው የከተማዋ አካል መሆን አለባቸው። በሚቀጥለው ጽሑፌ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የነበረውን የአዲስ አበባ ስፋትና ክፍለ ከተሞቿን አቀርባለሁ።

By: Achamyeleh Tamiru

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *