አጀንዳዬን አልቀይርም…!
ቲክቶከሩ ፍርድ ቤት ቀርቦ በፍርድ ቤት ፖሊስ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆበት የነበረ እና ፍርድቤቱም ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ፈቅዶለት የነበረ ቢሆንም በመሃል ግን በዛሬው ዕለት የኦሮሞ አባ ገዳዎች ነን ያሉ የምሥራቅ አሩሲ ኗሪ አባ ገዳዎች መኪና ሞልተው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የኦሮሙማ መንግሥታቸውን በገዳ ሥርዓት መሠረት ሽምግልና ጠይቀው ከፍርድ ቤት ቀጠሮ በፊት ዛሬ ምሽት ከፖሊስ ጣቢያ አማላጅ ሆነው፣ በዚያውም የገዳ ሥርዓት ማስታወቂያ ተሠርቶለት ተጠርጣሪው ከእስር እንዲወጣ መደረጉ ነው የተሰማው።
